የ20ኛው ግራንድ አፍሪካ የአመራርና የተቋማት ሽልማት እሁድ ይካሄዳል

You are currently viewing የ20ኛው ግራንድ አፍሪካ የአመራርና የተቋማት ሽልማት እሁድ ይካሄዳል
  • Post category:አፍሪካ

‎AMN ታኅሣሥ 11/2018 ዓ.ም

‎ ግራንድ የአፍሪካ የተቋማት እና የአመራር ሽልማት ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የልማት መስኮች የላቀ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማትና አመራሮች እውቅና የሚሰጥበት 20ኛው የሽልማት መርሃ-ግብር ታኅሣሥ 12 ቀን 2018 ዓ.ም የፊታችን እሁድ እንደሚካሄድ አስታወቀ።

‎የሽልማት ድርጅቱ በዋናነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአምራችነት እና በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ፣ ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ ስራዎችን የሰሩ ተቋማትንና መሪዎችን የሚያበረታታ ነው።

‎የድርጅቱ ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ግርማ በቀለ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል እንደገለጹት፣ ተሸላሚዎቹ የሚመረጡት ተቋሙ ባወጣው ጥብቅ መስፈርት መሠረት ነው ብለዋል።

‎ተቋማትና አመራሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ተቀባይነት እንዲኖራቸው ማድረግ፣ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት እንዲቀርብ ማበረታታት አላማ ያደረገ የእውቅና መርሀ ግብር መሆኑን ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

‎ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት (Import Substitution) ጥረትን ማገዝ አላማ ያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

‎በመርሃ ግብሩ ላይ የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ የቀድሞው የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ (ዶ/ር) እንደሚገኙ የገለፁት የድርጅቱ የሽልማት ዘርፎች እና ምዘና ስራ አስኪያጅ መለሰ መካሻ (ዶ/ር) ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚታደሙም ገልፀዋል።

‎የሽልማት መርሃ-ግብሩ በነገው ዕለት ታኅሣሥ 12 /2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን፣ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ (AMN) በቀጥታ ስርጭት ለተመልካች ይደርሳል፡፡

‎በሔለን ተስፋዬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review