በሀገራችን ድርጅቶችን እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አወዳድሮ ለሽልማት ማብቃት ባሕል ማድረጉ ሁሉንም ይጠቅማል ሲሉ ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የቀድሞ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ገለጹ።
ዶክተር ሙላቱ በመርሐ ግብሩ የማጠቃለያ ንግግራቸው እንደገለጹት፣ ከሁሉም በላይ አምራቾችን፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን እና ባለኃብቶችን ይጠቅማል ሲሉ ተናግረዋል።
ይህም የውድድር መንፈስ የሚፈጥር መሆኑን የገለጹት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ፣ ፉክክር ሲኖር ጥራት ያለው ምርት እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለተገልጋዮች ማድረስ ይቻላል ብለዋል።
ተጠቃሚው ማለት የመጨረሻው የተመረተን ምርትም ሆነ የተሰጠን አገልግሎት ተቀባይ ስለሚሆኑ፣ ጥራት ያላቸውን ምርት እና አገልግሎት ለህብረተሰቡም ሆነ ለተጠቃሚው በማድረስ በአገልግሎታችን እና በምርቶቻችን ጥራት የሚረካ ማህበረሰብ እና ሥርዓት እየገነባን መሆኑን ያሳያል ብለዋል ዶክተር ሙላቱ ።
ዶክተር ሙላቱ አክለው፣ ጥራት ያለው አገልግሎት እና ምርት ማምረትን ስርዓት ማድረግ ሲቻል፣ አገልግሎቶቹ፣ ከሀገር አልፈው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ በመሆን፣ የኢትYኦጵያ ምርቶች በዓለም ገበያም በጥራትም ፣ በዋጋም፣ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያግዝ ነው ብለዋል።
በዛሬው መርሓግብር የተሸለማችሁትም ሆነ ያልተሸለማችሁ ሁሉ እንደትልቅ ትምህርት መውሰድ ያለባችሁ ለምዘና ወደድርጅቶቻችሁ የመጡት ባለሞያዎች፣ የሰጡሓችሁን ግብረመልሶች ፣ ጠንካራ ጎኖቻችሁን እና መሻሻል ያለበትን በመለየት፣ ጠንካራ ሆናችሁ የተለያችሁበትን ጥንካሬን በማዳበር እና በማስቀጠል አሰራራችሁን በማሻሻል ፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ፣ ከውጪ ባለሞያዎችንም በማምጣት መሆን አለበት ብለዋል።
ትልቁ ፋይዳ እርስ በርስ አንዱ ድርጅት ከሌላኛው በመማማር የአገልግሎት ጥራትን እና ምርትን ማብዛት መሆኑን የገለጹት ዶከሩ፣ መወዳደር ማለት ትጠላልፎ፣ አንዱን ጥሎ ለብጫ መሮጥ አይደለም ያሉ ሲሆን፣ አቶ ገምሹ እንዳሉት አብሮ በመስራት መሆን አለበትም ብለዋል።
በወርቅነህ አቢዮ