አገልጋይ እና ተገልጋይን በቀጥታ የሚያገናኘዉ የእንጠያየቅ መድረክ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ተካሂዷል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የእንጠያየቅ መድረኩ ህዝብ መንግስትን የሚጠይቅበት መንግስትም ለጥያቄዎች ተገቢ ምላሾችን የሚሰጥበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በህዝብ ዘንድ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በትክክለኛዉ ሰአት ተገቢ ምላሽ ይሰጣቸዋል ያሉት አቶ ቴዎድሮስ መሰል መድረኮችም ተጠናክረዉ ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

በእንጠያየቅ መድረኩ ላይ ከተሳታፊዎቹ በተለያየ ዘርፎች በርካታ ጥያቄዎች ቀርበዋል፡፡
የክፍለ ከተማዉ የተቋማት የስራ ሀላፊዎችም ከኅብረተሰቡ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሾችንና ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡
በተመስገን ይመር