የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሀገር ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸው ተገለፀ

You are currently viewing የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሀገር ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸው ተገለፀ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN ታኅሣሥ 21 ቀን 2018 ዓ.ም

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሀገር ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናገሩ።

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለሀገር ግንባታ ያላቸው ፋይዳ በሚል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባደረጉት ንግግር ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች የሚወክሉትን ማሕበረሰብ ወክለው የሚሰሩ በመሆናቸው ይህ አሰራር ከመንግስት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ድርጅቶቹ ለሀገር ዲሞክራሲያዊ ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን ያረጋግጣል ብለዋል።

እንደ ሀገር የሚታለመውን የዳበረ ዲሞክራሲ ለመገንባት ከሲቪክ ማሕበራትና ከመንግስት ምን ይጠበቃል? እንዴትስ በቅንጅት ተናበውና ተቀናጅተው መስራት አለባቸው? የሚለውን በሚገባ በማስኬድ ዲሞክራሲን ማሳደግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ ከተማ በአዲስ አበባ የሚገኙ የሲቪክ ማህበራትን ለማሳተፍ የሚካሄዱ ትልልቅ ሀገራዊ ሁነቶችን በጋራና በሀላፊነት ማከናወን እንደሚገባ አቶ ሞገስ ገልፀዋል።

ውይይቱ “የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ለዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዋልታና ማገር ናቸው” በሚል መሪ ሃሳብ በየካ ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አለምፀሀይ ሽፈራውን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በንጉሱ በቃሉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review