ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የቡና ሃብት እና ህዝቡ ያለውን ታሪካዊ ቁረኝት ለዓለም ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ የሚዲያው ድርሻ ከፍተኛ ነው።
ኢትዮጵያዊያን ከቡና ሃብት ጋር ያላቸውን ባህላዊና ታሪካዊ ጥልቅ ቁርኝት ለዓለም በማስተዋወቅ እረገድ ከፍተኛ ድርሻ ያላቻው የመገናኛ ብዙሃን ቡድን፣ በኦሮሚያ ክልል ጂማ ዞን በሻሻ ወረዳ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።
በጂማ ዞን ጎማ ወረዳ በአጋሮ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ቀበሌዎች በሻሻ እና ጮጬ ከታ ሙዱጋ ከተጎበኙ ቡና አምራች ስፍራዎች መካከል ናቸው።

በእነኝህ አከባቢዎች ሰፋፊ የቡና አምራች አርሶ አደሮች የሚገኙ ሲሆን፣ በአከባቢው የቡና ምርት ሂደቶችን እንዲሁም ማህበረሰቡ ከቡና ጋር ያለውን መስተጋብር የቱሪዝም መዳረሻ ይሆኑ ዘንድ ከፍተኛ የማስተዋወቅና ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑን የጂማ ዞን ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኑሜሪ አባተማም ተናግረዋል።
በተለይም ቡና አምራች አርሶ አደሮች ምርታቸው በዓለም የቱሪዝም ገበያ ውስጥ ከፍተኛ እውቅና እንዲያገኝ በቀጥታ ለውጪ ገበያ እንዲያቀርቡ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ገልጸዋል።
በተጨማሪም አምራቾች ጥራት ያለው፣ በዓለም ቱሪዝም ገበያ ላይ ተመራጭ የሆነ የቡና ምርት እንዲያመርቱ ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑንም ተጠቁሟል።
በካሳሁን ማንጉዳ