አርሰናል በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የፊት አጥቂዎችን የሚያሰልፍበት መርሃ ግብር

You are currently viewing አርሰናል በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የፊት አጥቂዎችን የሚያሰልፍበት መርሃ ግብር

AMN ታኅሣሥ 24/2018

ከጉዳት ነጻ ለመሆን የተቃረበው አርሰናል ነገ ምሽት ቦርንማውዝን ይገጥማል፡፡

አርሰናል የፕሪምየር ሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ በአራት ነጥብ ልዩነት እየመራ ነው፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ በ20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ነገ ምሽት ከሁለት ሰዓት ተኩል ጀምሮ ከጠንካራው በርንማውዝ ጋር ከሜዳው ውጭ ይጫወታል፡፡

አርሰናልና በርንማውዝ 18 ጊዜ ተገናኝተው አርሰናል 12ቱን በማሸነፍ የበላይነቱን ይወስዳል፡፡ በርንማውዝ ሁለት ጊዜ ብቻ ሲረታ ቀሪ ሶስት ጨዋታዎችን በአቻ ውጤት ነው ያጠናቀቁት፡፡ ሁለቱ ክለቦች ባለፈው ዓመት በኤምሬትስ ላይ ተገናኝተው በርንማውዝ 2ለ1 ማሸነፉ የሚታወስ ነው፡፡

ነገ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ተኩል ጀምሮ በርንማውዝ ከተማ በሚገኘው ቪታሊቲ ስታድዬም በሚደረገው ጨዋታ አርሰናል የተሟላ ስብስብ ይዞ የሚገባበት ነው፡፡ ስለ ነገው ጨዋታ የተጠየቀው ሚካኤል አርቴታ የዛሬው ልምምድ ውጤትን እንጠብቅ ብሏል፡፡

አርሰናል በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሶስት የፊት አጥቂዎችን መጠቀም የሚችልበት ጨዋታ ነው የነገ ምሽቱ መርሃ ግብር፡፡ ጋብሬል ጀሱስ፣ ቪክቶር ጊዮኬሬሽና ካይ ሃቨርዝ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ናቸው፡፡ ‹‹ለቡድኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፣ ተደራራቢ መርሃ ግብር ስላለን በአጥቂ ስፍራ ሶስት ተጨዋቾችን መያዛችን ተጠቃሚ ያደርገናል›› ብሏል ስፔናዊ አሰልጣኝ አርቴታ ከክለቡ የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ባደረገው ቆይታ፡፡

ማክሰኞ ምሽት አስቶን ቪላን 4ለ1 ካሸነፉበት ጨዋታ ውጭ የሆነው ዴክላን ራይስ ከዛሬው ልምምድ በኋላ የመጨረሻ ምርመራ ተርጎለት ውሳኔ እንደሚተላለፍ አርቴታ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ ተከላካዮቹ ሪካርዶ ካላፊዮሪና ክሪስቲያን ሞስኩዌራ እንዲሁም ታዳጊው ማክስ ዶውማን ከነገው ጨዋታ ውጭ የሚሆኑ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

ክሪስ ካቫናህ በመሀል ዳኝነት የሚመሩትን ጨዋታ አርሰናል ካሸነፈ ለጊዜውም ቢሆን ከማንችስተር ሲቲ ጋር የሚኖረውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ያሰፋል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review