የከተማዋ ነዋሪዎችና እንግዶቿ በሰላም ወጥተው የሚገቡበት እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት ከተማ መፍጠር ተችሏል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄዱ ነው ።
በመድረኩ የየተቋማቱ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ አመራሮች ተሳትፈዋል::
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚህ ወቅት እንዳሉት ህብረተሰቡን በማሳተፍ እና በቴክኖሎጅ የተደገፈ ስራ በመሰራቱ የከተማዋ ነዋሪዎችና እንግዶቿ በሰላም ወጥተው የሚገቡባት ከተማን መፈጠር ተችሏል ብለዋል::
ባለፉት 6 ወራት ሃሰተኛ ሰነድ የሚያዘጋጁ ግለሰቦችን ጨምሮ ሕግ ወጥ መሳሪያ እና ገንዝብ አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለም ተናግረዋል::
ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ ማድረግ ሌላዉ በ6 ወሩ የተከናወነ ተግባር መሆኑንም ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል፡፡
ባለፉት 6 ወራት 33 ሺህ የሰላም ሰራዎት አባላት ስልጠና ወስደው ወደ ስራ መግባታቸዉንም ኃላፊዋ ተናግረዋል::
ህገ ወጥ የመሬት ወረራን፣ ህገ ወጥ ግንባታ እና የጎዳና ላይ ንግድን ከመከላከል አኳያም ተጨባጭ ዉጤቶች ተገኝተዋል ተብሏል::
በቴዎድሮስ ይሳ