ማይክል ካሪክ የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ለመሆን ሙሉ በሙሉ መስማማቱን ዘ አትሌቲከ ዘግቧል፡፡ ካሪክ በክለቡ የሚቆየው እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ብቻ ነው፡፡
ረዳቶቹን በራሱ የሚመርጠው ማይክል ካሪክ ነገ ስራውን በይፋ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ክለቡም የአሰልጣኙን ቅጥር ዛሬ ይፋ ያደርጋል ተብሏል፡፡
ከሁለት ውድድሮች በጊዜ የወጣው ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ የቀሩትን 17 ጨዋታዎች ብቻ ያከናውናል፡፡
በሸዋንግዛው ግርማ