AMN – ጥር 06/2018 ዓ.ም
ልጅ ሆኜ ስሜን ሳስበው ከታላቁ የፍቅር እሰከ መቃብር ደራሲ ሃዲስ ዓለማየሁ መመሳሰሉን ሳስብ ሰሙ ለኔ መጠሪያየ ብቻ ሳይሆን ለዓላማየም ስንቅ ነበር – ታዲያ አድጌ ዛሬ ላይ የታላቁን ደራሲ ስም ከማሲንቆ ጋር ቀላቀልኩት ነው ያለን – የማሲቆው ጥበበኛ ወጣት ሃዲስ ዓለማየሁ በመድረክ ስሙ ሃዲንቆ ።
የሃገራችን ታላላቅና ስመ ጥር ሙዚቃኞች በደገሱት የሙዚቃ ዝግጅት ከሚታዩት የባህላዊ ሙዚቃ መሳሪያዎች አንዱ የሆነውን ማሲንቆ ሲጫወት ከድምፃውያኑ እኩል የታዳሚውን ልብን ያርዳል ሃዲንቆ ።
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኖቤል ሽልማትን ለመቀበል ወደ ስፍራው ባቀኑበት ጊዜ አብረው ከተጓዙ ልዑካን መካከል አንዱ ነበር ።
ከሽልማቱ ባሻገር የመድረኩ ድምቀት በመሆን ከቤቲጂ ጋር ማሲንቆ ከፍ ብሎ በዓለም እንዲታይ በማድረግ በባህላዊ ሙዚቃዎቻችን ለካ እንዲህም መስራት ይቻላል በማለት የታዳሚውን እጅ በአፍ ያስከደነ ስራ ሰርቷል ።

ታዲያ ማሲንቆዬን ከራሴ ጋር አዋህጄ በራስ መገለጥ እኔ ሃዲንቆ ነኝ በማለት የባህላዊ ሙዚቃ በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲታወቅ እየሰራሁ ነው ሲል አጫውቶናል ።
የዓላማውን መንገድ አንድ ብሎ ጀምሯል፡፡ በዚህም የ2025 የአፍሪማ የአፍሪካ ጃዝ ምርጥ አርቲስት ዘርፍ አሸናፊ በመሆን ዋንጫውን በመቀበል ሀገሬን ማስጠራት ችያለሁ፤ እጅግም ደስተኛ ሆኛለሁ ነው ያለን ።
ለማሲንቆ እና ለባህላዊ ሙዚቃ ልዩ ፍቅር አለኝ ፤ዘርፉ እንዲዘምን እና ከቴክኖሎጂ ጋር እንዲጣመር በመስራት የሃገር ገፅታ ለማስተዋወቅ በጣም በርካታ ስራ ሰርቻለሁ፤ ይህንንም በትልልቅ መድረኮች ማሳየት ችያለሁ ይላል ሃዲንቆ ። ለዚህ ንግግሩ ብዙዎች ምስክሮች ናቸው ያለ ሃዲንቆ የአይደምቅም መድረኩ እያስባለ ይገኛል ።
አምስተርዳም ከ53 ሙዚቀኆች ጋር የሳንፎኒ ኦርኬስትራ የመድረክ ስራ ሰርቷል፡፡ እንዲሁም ከ21 በላይ ሃገራትን በመዞር የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድረጎ አስጠርቷል፡፡ በዚህም ኩራት እንደሚሰማው ነው የነገረን ።
ከታዋቂው የጃዝ ንጉስ ሙላቱ አስታጥቄ ጋር በተለያዩ ሃገራት ስራዎችን የማቅረብ ዕድል እንደገጠመው እና ይህም ከታላላቆች የሙያ አባቶች ልምድ እና ትምህርት እንዲያገኝ ረድቶታል።
ይህን ሁሉ ሂደት የ2025 የአፍሪማ ምርጥ የጃዝ አርቲስት ዕጩ እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ታዲያ በዕጩነት ብቻ አልቀረም በታጨበት የምርጥ ጃዝ አርቲስት ስመ ጥር ከሆኑት ሪቻርድ ቦና እና ማዴ ኩቲ /የፌላ ኩቲ/ ቤተሰብ ጋር በመወዳደር በአንደኝነት በማሸነፍ የሀገሬ ሙዚቃ ተሽሎ በመገኘቱ በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያዬ ከፍ ብላ እንድትጠራ አድርጊያለሁ፤ በዚህም እጅግ ከፍተኛ ኩራት ተሰምቶኛል ሲል ስሜቱን አጋርቶናል ።
በአፍሪማ ያገኘሁት ውጤት እና ሽልማት ለኔ ብቻ ሳይሆን ነገን ተሰፋ ለሚያደርጉ የማሲንቆ ተጫዋቾች ብዙ መነቃቃትን የሚፈጥር ነው ።

በአፍሪማ 2025 ከሃዲንቆ በተጨማሪ ድምፃዊ ቬሮኒካና ዊሃ በተለየያ ዘርፍ ተወዳድረው በማሸነፍ የሀገራቸውን ስም በአፍሪካ እንዲናኝ አድረገዋል፡፡ የዚህ ስሜትስ ምን ይመስል ነበር ብለን ላነሳንለት ጥያቄ ምላሽ የሰጠው ሃዲንቆ ሙዚቃ የቡድን ስራ ነው፡፡ ምንም እንኳን በተለየያ ዘርፍ ታጭተን ብናሸንፍም በጋራ ሃገርን በማስጠራታችን ደስታዬ ወደር አልነበረም፤ እናም ይህንን ሽልማት እንዳሸንፍ ከጎኔ ለነበራቸሁ ሁሉ በኔ ውስጥ የሃገራችንን ባህላዊ ሙዚቃ በዓለም መድረክ እንዲተዋወቅና ዕውቅና እንዲኖረው አድርጋችኋልና ፈጣሪ ያክብርልኝ ሲል ከኤ ኤም ኤን ዲጂታል ጋር በነበረው ቆይታ ሃሳቡን አጋርቶናል ።
ውድ ተከታዮቻችን እናንተስ ሃዲንቆ በመሰንቆ ተጫዋችነቱ ያገኘው ሽልማት ምን ስሜት ፈጠረባችሁ በሃዲንቆ የማሰንቆ አጨዋወትስ ምን ሃሳብ አላችሁ ሃሳባችሁን አጋሩን
በያለው ጌታነህ
Wendi Addis TV, [1/14/2026 5:36 PM]
ዌብ ላይ ጫኑት