AMN – መስከረም 28/ 2019

የ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ይገኛል።
በጉባዔው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት ዕጩ የካቢኔ አባላትን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የምክር ቤቱ አባላትም በቀረቡ ዕጩዎች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን ከሰጡ በኋላ በሙሉ ድምፅ አጽድቀውታል።

ሹመታቸው የጸደቀላቸው የካቢኔ አባላትም በምክር ቤቱ አባላት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።
በበረከት ጌታቸው