የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ የማገልገልን ዕድል ዳግም አግኝቻለሁ- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – መስከረም 28/2019 ዓ.ም

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅራቢነት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ፣ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኜ የማገልገልን ዕድል ዳግም አግኝቻለሁ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ የተቀበልኩት ሕዝብና ሀገርን የማገልገል ከባድ ኃላፊነት ነውም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን በምችለው ሁሉ በማገልገል ኃላፊነቴን እንድወጣ የሁላችሁም ድጋፍ እና ጸሎት አስፈላጊ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review