ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው bደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሱርማ ወረዳ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ አደረጉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ በክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሱርማ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የተገነባ ትምህርት ቤት ርክክብ ሥነሥርዓት ላይ ስንገኝ በአካባቢው የትምህርት መስክ እድገት ረገድ ዐቢይ ተግባር በመሆኑ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።
ትምህርት ቤቱ በቀዳሚነት ከአካባቢው ለሚመጡ ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት በመሆን እንደሚያገለግልም ገልጸዋል።
ግቢው ማደሪያ ክፍሎችን፣ መማሪያ ክፍሎችን፣ በፀሃይ ኃይል የሚሰሩ በቂ ኮምፒውተሮች ያሉት የኮምፒውተር ላብራቶሪ፣ የንፁህ ውሃ ጉድጓድ፣ የተሟላ የምግብ ማብሰያ ክፍል፣ ቤተ መፃሕፍት እና የአስተዳደር ሕንፃን አካትቶ የተገነባ መሆኑንም አመላክተዋል።
ይኽ ምሉዕነት ያለው የትምህርት ከባቢ የተማሪዎችን አካዳሚያዊ ልህቀት እና ደኅንነት ለማረጋገጥ ታስቦበት የተሰራ፣ ለወጣት ተማሪ ልጆቻችን ሁሉን አቀፍ እድገት አዲስ እድል የፈጠረ ተቋም ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡