ሴኔጋል ሞሮኮን በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን አሸነፈች

You are currently viewing ሴኔጋል ሞሮኮን በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን አሸነፈች

AMN ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም

35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በሴኔጋል አሸናፊነት ተጠናቋል።

በድራማ የታጀበውን የፍፃሜ ጨዋታ ሴኔጋል አዘጋጇ ሞሮኮን 1ለ0 አሸንፋለች።

የጨዋታው መደበኛ 90 ደቂቃ ሊጠናቀቅ ጭማሪው ደቂቃ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት ያገኘችው ሞሮኮ ሳትጠቀምበት ቀርታለች።

ፍፁም ቅጣት ምቱ መሰጠቱ ያላስደሰታቸው የሴኔጋል ተጫዋቾች በአሰልጣኛቸው ፓፔ ቲያው ተመርተው ጨዋታ አቋርጠው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተው ነበር።

ነገር ግን በሳዲዮ ማኔ ውትወታ ወደ ሜዳ በመመለስ ጨዋታውን ቀጥለዋል።

ከ15 ደቂቃ በላይ ቆይቶ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት የመታው ብራሂም ዲያዝ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

በውድድሩ የሞሮኮ ብርሃን የነበረው ዲያዝ ከ50 ዓመት በኋላ ሀገሩ የአፍሪካ ዋንጫ የምታነሳበትን እድል አጨልሟል።

በጭማሪው ደቂቃ ሴኔጋል በአማካዩ ፓፔ ጌይ ድንቅ ግብ ጨዋታውን 1ለ0 ማሸነፍ ችላለች። ለሁለተኛ ጊዜም የአህጉሪቱ የበላይ ሆናለች።

ከ22 ዓመት በኋላ ለፍፃሜ የደረሰችው ሞሮኮ ከአምስት አስርት ዓመታት በኋላ ዋንጫ የማንሳት ህልሟ ከስሟል።

ለአንድ ወር የዘለቀው የ2025ቱ የአፍሪካ ዋኝጫ በዚህ መልኩ ባልተጠበቀ ድራማ ታጅቦ ተጠናቋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review