አደገኛ እፅዋትን ከነአዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

You are currently viewing አደገኛ እፅዋትን ከነአዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

‎AMN- ጥር 13/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከ445 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝኑ አደገኛ ዕፅዋትን ከነአዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።

‌‎የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ፀረ-ፈንጅና አደገኛ ዕፅዋት ዝውውር ቁጥጥር መምሪያ፣ ባለፉት ስድስት ወራት ከ445 ኪሎ ግራም በላይ አደገኛ ዕፅዋት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገልጿል።

ይህም ከ2017 ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የዝውውሩ መጠን መቀነሱን ጠቅሶ፣ የቁጥጥር ሂደቱ ዘመናዊ አሠራር የተከተለ በመሆኑ ውጤታማነቱ መጨመሩን አመልክቷል።

‎በተካሄዱ የአደገኛ ዕፅዋት ቁጥጥር ስራዎች ኮኬይንና ካናቢስ የተባሉ አደገኛ ዕፅዋት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የገለፀው ፀረ-ፈንጅና አደገኛ እፅዋት ዝውውር ቁጥጥር መምሪያ፣ በተከናወኑ ጠንካራ የፍተሻና የክትትል ሥራዎች የ13 ሀገራት ዜግነት ያላቸው 19 ግለሰቦች በዝውውሩ ሲሳተፉ መያዛቸውን ገልጿል።

የአደንዛዥ ዕፅዋት ዝውውር ወንጀል በቁጥጥር ሥር ባዋላቸው ተጠርጣሪዎች ላይም ምርመራውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሠራው ዘገባ በ1996 የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ 1(ለ) ሥር የተደነገገውን በመተላለፍ በአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር ወንጀል ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ማስቀጣት መቻሉን በማስታወስ በቀጣይም አደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአዘዋዋሪዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review