ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከ ማንችስተር ሲቲ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፉልሃም፦ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች

You are currently viewing ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከ ማንችስተር ሲቲ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ ከ ፉልሃም፦ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታዎች

AMN ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የ24ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሐግብር ዛሬም ቀጥሎ አራት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።

ማንችስተር ሲቲ ወደ ሚቸገርበት ቶተንሃም ስታዲየም አቅንቶ የሰሜን ለንደኑን ክለብ ይገጥማል።

ፔፕ ጋርዲዮላ ማንችስተር ሲቲ ከተረከበ በኋላ በፕሪሚየር ሊጉ እንደ ቶተንሃም የፈተነው ቡድን የለም። ስፔናዊ አሰልጣኝ በቶተንሃም ስምንት ሽንፈት አስመዝግቧል። ፔፕ በየትኛውም ቡድን ይህን ያህል ጊዜ በሊግ ጨዋታ አልተሸነፈም።

ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ በኢትሃድ ባደረጉት ጨዋታ የቶማስ ፍራንኩ ቶተንሃም 2ለ0 ማሸነፉም ይታወሳል።

አሁንም አስተማማኝ ደረጃ ላይ የማይገኘው ሲቲ ትናንት አርሰናል ሊድስ ዩናይትድን ማሸነፉን ተከትሎ ወደ ሰባት የሰፋውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ይጠበቅበታል።

ቶተንሃም ምንም እንኳን ማንችስተር ሲቲ ላይ በቅርብ ዓመታት ጥሩ ክብረወሰን ቢኖረውም ዘንድሮ በሜዳው ያስመዘገበው ውጤት ደካማ ነው። ከ11 ጨዋታ ዘጠኝ ነጥብ ብቻ ነው ማግኘት የቻለው። በዚህ ቁጥር የሚበልጠው ዎልቭስን ብቻ ነው።

የሁለቱ ክለቦች ተጠባቂ ጨዋታ ምሽት 1:30 ላይ ይጀምራል።

በሌላ ጨዋታ ማይካል ካሪክን ከሾመ በኋላ ጥሩ ጉዞ ላይ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ፉልሃምን በኦልድትራፎርድ 11 ሰዓት ላይ ያስተናግዳል።

ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ላይ ካስመዘገበው ተከታታይ ድል መነሻ የዛሬውንም ጨዋታ ያሸንፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ 11 ሰዓት ላይ አስቶንቪላ ከ ብሬንትፎርድ ፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ክሪስታል ፓላስ ይጫወታሉ።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review