በዚህም መሰረት፦
1ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አሁናዊ የከተማዋ ፈጣን ዕድገት እና ለውጥ መሰረት ያደረገ በአምስት (5) ዋና ደረጃዎች እና በሰላሳ (30) ንኡሳን ደረጃዎች የቦታ ደረጃ (Land grading) ጥናት ቀርቦ፣ በቀረበው ደረጃ መሰረት የተሻሻለ የሊዝ መነሻ ዋጋ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
2ኛ. የከተማዋን የግዢን እና ንብረት አስተዳደር ሂደት እና ስርዓት ለማዘመን፣ የስራ ቅልጥፍናን ለማላቅ እንዲሁም ንብረትን በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ታሳቢ ያደረገ “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ” ላይ ተወያይቶ እንዲፀድቅ ለምክርቤት እንዲላክ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
3ኛ. ሃገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ምደባ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል። – የከንቲባ ጽ/ቤት