አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተምሳሌት የሚሆኑ የሚዲያ ሥራዎችን እየሠራ ነው – ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ)

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ተምሳሌት የሚሆኑ የሚዲያ ሥራዎችን እየሠራ ነው – ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ)

AMN – የካቲት 1/2018 ዓ.ም.

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የሚያቀርባቸው ፕሮግራሞች የሕዝብን ድምጽ ወደ ተግባራዊ ለውጥ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት መሆናቸውን የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) ገለጹ።

ነብዩ ባዬ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሥራዎችን በተለየ ሁኔታ ማመስገን እንደሚፈልጉ ገልጸው፣ በተለይም “ዋርካ” እና “አገልጋይ” የተሰኙት ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ሚዲያ ታሪክ አዲስ አቅጣጫ የጠቆሙ መሆናቸውን አብራርተዋል።

እነዚህ ፕሮግራሞች የሚዲያ ይዘት (Media Content) ተጠያቂነትን እንዲያስከትል በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና መጫዎታቸውን ገልጸዋል።

የሚዲያ ይዘት የሕዝብን ድምጽ ወስዶ ወደ እርምጃና ወደ ተግባር የሚመራ አፈጻጸም ሲኖረው መመልከት ትልቅ ምስጋና ያስገኝለታል በማለት ተቋሙ ላሳየው ቁርጠኝነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ተቋሙ ከወቅታዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ባሻገር፣ በመዝናኛና በኪነ-ጥበብ ውድድሮች ዘርፍ የጀመራቸው አዳዲስ ፕሮግራሞች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል። እነዚህ በጥበብ ላይ ያተኮሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ይበልጥ እንዲጎለብቱም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ለሠሩት ውጤታማ ሥራ ምስጋናቸውን በማቅረብ፣ ሚዲያው የጀመረውን ሕዝባዊ ወገንተኝነትና ሙያዊ ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review