በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 1/2018 ዓ.ም

ዛሬ በ24/7 የሥራ ባሕል የከተማችንን የኮሪደር ልማት ሥራዎች እያፋጠኑ ከሚገኙ ታታሪ ሰራተኞች ጋር ማዕድ በማጋራት አበረታተናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ እነዚህ ብርቱ ሰራተኞች በተለያዩ የግንባታ ሳይቶች፤ በተለይም በካዛንቺስ የሕፃናት ዓለም፣ በስፖርት ፓርክ እና በአዲስ አኳሪየም ግንባታዎች፣ እንዲሁም ከኡራኤል እስከ ቦሌ ቪ.አይ.ፒ (VIP)፣ ከኢንግሊዝ ኢምባሲ 22 እስከ ቦሌ ፍሬንድሺፕ ሆቴል እና ከውኃ ልማት እስከ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ እየተከናወኑ ባሉ መጠነ ሰፊ የኮሪደር ልማት አያያዥ መስመሮች ላይ ሌት ተቀን የሚተጉ ናቸው ብለዋል።

በከፍተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ለከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት በእውቀታቸውና በጉልበታቸው እያበረከቱ ላለው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን፤ አዲስ አበባ ሁልጊዜም ታመሰግናችኋለች በማለትም አክለዋል።

በከተማችሁ መልማት በመደሰት ሁሌ በማዕድ ማጋራት እና እነዚህን ብርቱ ሰራተኞ በማበረታት መርሃ ግብር እየተሳተፋችሁ ላላችሁ ባለሀብቶች በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review