AMN- የካቲት 8/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ንቅናቄ እና የከተሞች ልማት በሁሉም አፍሪካዊያን ዘንድ ሊቀመር የሚገባ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ ተናገሩ፡፡
አፍሪካ በተፈጥሯዊ ክስተቶች እና በሰዉ ሰራሽ ችግሮች እየተፈተነች መሆኑንም የህብረቱ ሊቀመንበር ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ባለፋት አመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጭነት በመንግስት እና በህዝብ ቅንጅት እዉን ያደረገችወዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ንቅናቄ ለዓለም ምሳሌ የሚሆን ነዉ ብለዋል፡፡

በሌላ መልኩ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ የሱፍ ኢትዮጵያ በከተማ ልማት ዘርፍ የሰራቻቸዉን ስራዎችን አወድሰዋል፡፡
አዲስ አበባን የከተሞች መዘመን ማሳያ እና አምሳያ አድርገዉ ያነሱት ማህሙድ አሊ የሱፍ ከተማዋ የአፍሪካ ብቻ ሳይሆን የዓለም የስበት ማዕከል እየሆነች ነዉ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ አህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶች ይደረጋሉ ያሉም ሲሆን በአህጉሩ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረገዉ ኮፕ32 ተጠባቂ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
በተመስገን ይመር