አድዋ- የነፃነት ፋና ወጊ

You are currently viewing አድዋ- የነፃነት ፋና ወጊ
  • Post category:ታሪክ

AMN- የካቲት 19/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለቅኝ ገዢዎች አልንበረከክም በማለት፣ በብቸኝነት ተዋግቶ ዓለምን ያስገረመ ታላቅ ገድል ፈጽሟል።

ወራሪውን የጣሊያን ጦር በማሸነፍ ለአፍሪካውያን የነፃነት ፋና ወጊና አርአያ መሆን የቻለው ይህ ታሪካዊ ድል ከተመዘገበ እነሆ ዘንድሮ 130ኛ ዓመቱን አስቆጠረ።

የበዓሉን መታሰቢያ አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንደገለጹት፤ አድዋ የጀግንነትና የኩራት ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ፣ የአሁኑ ትውልድ ጠንክሮ በመስራትና ሀገርን በመውደድ ከአባቶቹ ሊማርበት የሚገባ የታሪክ አሻራ ነው።

ለኤ ኤም ኤን አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ማሙሸት እሸቱ፣ የአድዋ ድል የጀግንነታችንና የኩራታችን ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው፣ ተተኪው ትውልድም ከታሪኩና ከተፈጥሮ ሀብቱ በመነሳት ሀገርን መውደድና ጠንክሮ መስራትን ከአባቶቹ ሊማር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ወጣት ሚኪያስ ተስፋዬ በበኩሉ፣ አባቶች ተዋግተው ሀገርን በአንድነት አጽንተው ባያቆዩልን ኖሮ ዛሬ ለምንገኝበት ደረጃ እንደማንበቃ ጠቅሶ፣ ትውልዱ ድሉን በክብር እያስታወሰ ሊዘክረው እንደሚገባ ተናግሯል።

ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ሳህሌ ሉክሱ እንዳሉት፣ ትውልዱ ከዚህ ድል ብርታትን በመውሰድ በእውቀቱና በጉልበቱ ጠንክሮ በመስራት የሀገሪቱን ታሪክ በላቀ ደረጃ ማስቀጠል አለበት።

አቶ አለሙ ኢተፋ እና አቶ ፉፋ ናደው በበኩላቸው፣ የአሁኑ ትውልድ የሀገርን ክብርና የሕዝብን ሉዓላዊነት አሳልፎ ባለመስጠት፣ ከአድዋ ጀግንነት የተማረውን አኩሪ ታሪክ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአድዋ ድል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ የገለጹ ሲሆን፣ የአሁኑ ትውልድ ይህንን ነፃነት ያስረከቡትን አባቶች ታሪክ በሥራና በእውቀት ሊዘክረው እንደሚገባ ተናግረዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review