በአዘርባጃን ባኩ ዛጉልባ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከተካሄደው ውይይት በመቀጠል፣ ሁለቱ መሪዎች በመከላከያ እና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነዶች የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

You are currently viewing በአዘርባጃን ባኩ ዛጉልባ ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግሥት ከተካሄደው ውይይት በመቀጠል፣ ሁለቱ መሪዎች በመከላከያ እና በበርካታ መስኮች በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነዶች የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል።

‎ከተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ (COP32) ማዘጋጀት፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ-ሙስና ትብብር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው።

‎በሌላ በኩል የአዘርባጃንን የአገልግሎት ዘርፍ ዝመናን በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው ተቋም “አሳን” (ASAN) እና በኢትዮጵያ የመሶብ አገልግሎት መካከል በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።

‎እነዚህ ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ እና እንደሚያሰፋፉ ይጠበቃል። – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review