ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) 24ኛዉን የአፍሪካ ህብረት ቀንን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) 24ኛዉን የአፍሪካ ህብረት ቀንን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

AMN ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) 24ኛዉን የአፍሪካ ህብረት ቀንን ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያ ከቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የአፍሪካን አህጉራዊ ጉዞ በጽኑ በመደገፍ ድምጽ ሆና ቆይታለች ብለዋል፡፡

አዲስ አበባም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና መኖሪያ መሆን መቻሏን ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

24ኛዉ የአፍሪካ ህብረት ቀን ስናከብር፣ የተዋሃደች እና የበለጸገች አፍሪካን ራዕይ እንደገና የምናረጋግጥ ነዉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደፊት ለምናመጣው የጋራ እድገትም እንተጋለን ብለዋል፡፡

እንደ አፍሪካ ህብረት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዲጂታል ጤና ቻምፒዮንነቴ መጠን፣ የአፍሪካ መሪዎችን እና ወጣቶችን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን እንዲቀበሉ እና ዲጂታል የወደፊት እጣ ፈንታቸዉን በራሳቸዉ ቃላት እንዲቀርጹ ጥሪ አቀርበዋል።

ኢትዮጵያም ከሌሎች የአፍሪካ ወንድሞቿ ጋር በመሆን ያንን የወደፊት ጊዜ ለመገንባት ዝግጁ ነች በማለት መልካም የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review