AMN – መጋቢት 6/2018 ዓ.ም.
መቄዶንያ ተስፋ የሚቀጠልበትና የሕይወት ሙሉነት የሚረጋገጥበት ሥፍራ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጎ ዓላማ ካለው ከዚህ ተቋም ጎን ሊቆም ይገባል በማለት ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ተናገሩ።
የመቄዶንያ የሁለተኛ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በተገኙበት በመቄዶንያ አዲስ ስቱዲዮ ተጀምሯል።
መረዳዳት እና መደጋገፍ የኢትዮጵያንውያን ባሕል ቢሆንም መቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል እያከናወነው ያለው ተግባር አስደናቂ ነው በለዋል ፕሬዘደንቱ።
በመገንባት ላይ የሚገኘውን የመቄዶንያ ሕንጻ የጎበኙት ፕሬዝደንቱ ግንባታው አስደናቂ መሆኑን ገልጸው ከተግባር በፊት ሀሳብ ሊደነቅ ይገባል በማለት የመቄዶንያ አረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማሗዕከል መሥራች ለሆኑት ቢኒያም በለጠ አክብሮታቸውን ተናግረዋል።

ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት በዋናነት የመንግስት ተግባር መሆኑን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ የማኅበረሰብን ህይወት በዘላቂነት ለመፍታት ጠንካራ እና ራዕይ ያለው አመራር ወሳኝ ነው ጠንክሮ መስራት እና የስራ ባህልን መቀየር ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ ደግሞ አዲስ አበባ ሕያው ምስክር ናት ብለዋል።
ማኅበራዊ ኃላፊነት በዋናነት የመንግስት ተግባር በመሆኑ የማኅበረሰብን ሕይወት በዘላቂነት ለመፍታት ራዕይ ያለው አመራርና ጠንካራ የሥራ ባሕልን መቀየር ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ አዲስ አበባ ሕያው ምስክር ናት ብለዋል።
የሕይወት ሙሉነት የሚረጋገጠው ካለ ቆርሶ በማካፈል በመሆኑ መቄዶንያን በመደገፍ የኅሊናም የነፍስም በረከት አግኙ ሲሉ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በቤተልሔም አየነው