AMN መጋቢት 8/2018 ዓ.ም
ቻይና በደቡብ ኢትዮጵያ ጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወትና ንብረታቸዉን ባጡ ዜጎች የተሰማትን ሃዘን ገልጻለች፡፡
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን በኢትዮጵያ የደረሰውን የተፈጥሮ አደጋ አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ቻይና በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ትልቅ ሃዘን እንደተሰማት ገልጸዋል፡፡ ቻይና ለተጎጂ ቤተሰቦች ልባዊ መጽናናትን ትመኛለች ብለዋል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸዉ ነዋሪዎች ችግሩን ተቋቁመው በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንደሚመለሱ እምነታችን የጸና ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ቻይና በአደጋው ለተጎዱ ወገኖችና ለድህረ-አደጋ መልሶ ግንባታ ስራዎች የተቻለዉን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡