AMN- መጋቢት 13/2018 ዓ.ም
በካራባኦ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲ አርሰናልን 2ለ0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆነ። ከ88ሺ በላይ ተመልካቾች በዌምብሌይ በታደሙበት ጨዋታ ሲቲ ከእረፍት መልስ በኒኮ ኦራይሊ ሁለት ግቦች ባለ ድል መሆን ችሏል።
የጨዋታው የመጀመሪያ ግብ ሲቆጠር የአርሰናል ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ ስህተት የጎላ ነበር። አርሰናል በእንግሊዝ ታሪክ አራት ዋንጫ አሸንፎ ታሪክ የመስራት ዕድሉ አብቅቷል።
ማንችስተር ሲቲ ዘጠነኛ የካራባኦ ዋንጫውን አሳክቷል። ከእነዚህ ዋንጫዎች አምስቱን ያሸነፈው ፔፕ ጋርዲዮላ ነው። በዚህም አምስት የካራባኦ ዋንጫ ያነሳ ብቸኛው አሰልጣኝ በመሆን ታሪክ ሰርቷል።
አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በፕሪምየር ሊጉ እና ኤፍ ኤ ካፕ ሌላ ፉክክር ይጠብቃቸዋል። ፕሪምየር ሊጉን አርሰናል አንድ ተጨማሪ ጨዋታ አድርጎ በዘጠኝ ነጥብ ይመራል። በኤፍ ኤ ካፕ ደግሞ ሁለቱም ሩብ ፍፃሜ ላይ ይገኛሉ።
በሸዋንግዛው ግርማ