አዲስ አበባ – የአፍሪካ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ቀዳሚ መዳረሻ

You are currently viewing አዲስ አበባ – የአፍሪካ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ቀዳሚ መዳረሻ

AMN – መጋቢት 22 /2018 ዓ.ም

ባለፉት ስምንት ዓመታት አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲናነቷን የሚያጠናክሩ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በማከናወን የዓለም አቀፍ ኹነቶች ስኬታማ አስተናጋጅ መሆኗን አስመስክራለች።

ከተማዋ ትላልቅ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ጉባኤዎችን እያስተናገደች የምትገኝ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማዋን ለውጥ ተከትሎ በግማሽ አመት ብቻ እስከ 15ዐ ኮንፈረንሶችን አስተናግዳለች።

ለዚህ ስኬት ደግሞ ዘመናዊ አዳራሾችን የያዘው የአድዋ መታሰቢያ እና አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል የመሰሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

እነዚህ አዳዲስ ማዕከላት ከአንጋፋዎቹ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዳራሾች ጋር በመቀናጀት ከተማዋ በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን የመቀበል አቅሟን ከፍ አድርገውታል።

ከእነዚህም ጎን ለጎን እንደ ስካይላይት ያሉ ግዙፍ ሆቴሎች መገንባት የከተማዋ ዕንግዶች የማረፊያ አቅምን በእጅጉ ከፍ እንዲለ አድርጎታል።

ይህ በዘርፉ የታየው ለውጥ ለከተማዋ ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎችን አስገኝቷል። በኢኮኖሚ ረገድ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ከማስመዝገቡም ባለፈ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሆቴል፣ በትራንስፖርትና በበተለያዩ የመስተንግዶ ዘርፎች ለተሰማሩ ሰፊ የስራ ዕድልን ፈጥሯል።

በተጨማሪም እንደ አንድነትና ወዳጅነት ያሉ አዳዲስ ፓርኮች ለእንግዶች ማራኪ የመዝናኛ አማራጭ በመሆን የከተማዋን ገጽታና የቱሪዝም ፍሰት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረውታል።

በአጠቃላይ አዲስ አበባ ባለፉት ስምንት ዓመታት ባሳየችው አስደናቂ የለውጥ ጉዞ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ዘርፍ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ተመራጭ መዳረሻ መሆኗን አረጋግጣለች።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review