በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን ወደ 253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ አሳድገናል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN- ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

በ2009 ዓ.ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ወደ 253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ አሳድገናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች በማሕበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ፣ እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በቀን 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ የማምረት አቅማችን አሁን ላይ ወደ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ ማሳደግ ችለናል ብለዋል።

በተለይ ዛሬ የመረቅናቸው ደግሞ የማምረት አቅምን ከማሳደግ ባሻገር አለም የደረሰበትን እጅግ የረቀቁ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በዘላቂነት ፈርቀዳጅ ሚና አላቸው ሲሉ አብራርተዋል።

ከንቲባዋ በመልዕክታቸው ፣ አዲስ አበባ እንደ ስሟ ውብ፣ አዲስ ፥ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ በማድረግ እና አገልግሎትን የሚያሳልጡ ዘመናዊ መሰረተ ልማቶችን ከዛሬ አልፎ ለትውልድ የምታሸጋግር ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review