አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ ፦ የኮሚኒቲ ሺልድ ፍልሚያ

AMN- ነሐሴ 10/2018 ዓ.ም

May be an image of football, soccer and text that says 'THE FA COMMUNIT NITY SHIELD CoTил CommunityShield ty Shield Arsenal Man City 16 August 2026 Sunday 10:00pm 10:00pmKick-Off Kick-Off Ameri Lecgue Premier PremierLeagureAmin PremierLonguPeterLinp ረመማራሪ Premer astro astro Grandstand Arsenal 0 Premier PremierLeogue League Astro Grandstand (CH810) & Astro Premier League (CH811) •• e лapeл " ስ 2'

በእንግሊዝ የውድድር ዓመቱ ማሟሻ ተደርጎ የሚቆጠረው የኮሚኒቲ ሺልድ የዋንጫ ጨዋታ ዛሬ ይደረጋል።

ጨዋታው የፕሪሚየር ሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ አሸናፊ ቡድኖችን የሚያፋልም ነው። ሁለቱንም ዋንጫዋች አንድ ቡድን ካነሳ በሊጉ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀ ቡድን የጨዋታው ተሳታፊ ሆኗል።

ዘንድሮ የፕሪምየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል የኤፍ ኤ ካፕ ባለድሉ ማንችስተር ሲቲን ይገጥማል።

ጨዋታው የዋንጫ ቢሆንም በእንግሊዝ የሚሰጠው ቦታ ግን ዝቅ ያለ ነው። አንዳንዶች ትንሽ ጠንከር ያለ የወዳጅነት ጨዋታ አድርገው ይቆጥሩታል። ዋንጫውም እንደሌሎቹ ቦታ ተሰጥቶት ከቁጥር የሚገባበት ጊዜ የለም።

እንዲህም ቢሆን ክለቦች ዋንጫውን የራሳቸው ለማድረግ ትልቅ ጥረት ያደርጋሉ። ዛሬ አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ 104ኛውን የኮሚኒቲ ሺልድ ሲያከናውኑ ትልቁ ግባቸው ጋሻ መሳይ ዋንጫውን ማንሳት ነው።

ከ22 ዓመት በኋላ የሊግ ዋንጫውን አንስቶ ለዛሬው ጨዋታ የበቃው አርሰናል 17 ጊዜ የኮሚኒቲ ሺልድን አሸንፏል። የሰሜን ለንደኑ ክለብ የሚበለጠው 21 ጊዜ ባለድል በሆነው ማንችስተር ዩናይትድ ብቻ ነው። መድፈኞቹ ለመጨረሻ ጊዜ የኮሚኒቲ ሺልድ ያነሱት ማንችስተር ሲቲን በመለያ ምት በማሸነፍ ነበር።

ማንችስተር ሲቲ በአንፃሩ ሰባት ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል። ሲቲ ለመጨረሻ ጊዜ ኮሚኒቲ ሺልድን ያሸነፈው በ2024 ማንችስተር ዩናይትድን በመለያ ምት በመርታት እንደነበር ይታወሳል።

በዛሬው ጨዋታ በአርሰናል በኩል ቡካዮ ሳካ ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ማርቲን ዙብሜንዲ እንዲሁም አዲስ ፈራሚው ቡርኖ ጉማይሬሽ ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በማንችስተር ሲቲ በኩል ደግሞ ኧርሊንግ ሀላንድ የመጫወት ዕድል አለው። አዲስ ፈራሚው ኤሊዮት አንደርሰንም ይሳተፋል። አማካዩ ሮድሪ ግን ይገባል ተብሎ አይጠበቅም።

በካርዲፍ ሚሊኒየም ስታዲየም የሚከናወነው ጨዋታ 11 ሰዓት ላይ ይጀምራል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review