AMN- መጋቢት 23/2018 ዓ.ም
በጠባብ መንገዶች፣ በተጎሳቆሉ አካባቢዎችና በቆሸሹ ፍሳሾች የምትገለጸዋ አዲስ አበባ፣ ዛሬ የለችም፡፡
አዲስ አበባ አሁን ስሟን የሚመጥን ለውጥ ላይ ትገኛለች፤ የኮሪደር ልማቱ ያመጣው ውበት እና የተገነቡት ግዙፍ ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ወደ ዓለም አቀፍ ከተሜነት ደረጃ ከፍ አድርገዋታል።
የከተማዋ መጥፎ ገጽታ የሆኑት፣ የቆሸሹ ፍሳሾችና ቆሻሻዎች ይከማቹባቸው የነበሩ ሥፍራዎች ዛሬ መልካቸውን ቀይረው የውበቷ ማሳያ ሆነዋል።
እነዚህ ዳግም የለሙ ሥፍራዎች ወደ ማራኪ የአረንጓዴ ቦታዎች፣ ዘመናዊ የመዝናኛ ፓርኮችና የፏፏቴ መስኮች በመለወጣቸው የከተማዋን የአየር ንብረት ከማሻሻል ባለፈ፣ ለነዋሪዎቿ የአእምሮ ዕረፍትና የአካል ማረፊያ መሆን ችለዋል።

ይህ ስኬት አዲስ አበባን የሥራ ብቻ ሳይሆን የኑሮ ተስማሚነቷ የተረጋገጠ ዓለም አቀፍ ከተማ የማድረግ ጉዞ አንድ ማሳያ ነው። በከተማዋ ወንዞች ዳርቻ ይፈሱ የነበሩ የቆሸሹ ፍሳሾች ታሪክ ሆነው ቀርተዋል።
በምትካቸውም ድንቅ መዝናኛዎችና ለዓይን የሚማርኩ የአረንጓዴ መናፈሻዎች ተተክተዋል። አዲስ አበባ ዛሬ በተግባር የታየ የከተሜነት ለውጥ ተምሳሌት ሆናለች።
ይህ ለውጥ ለከተማዋ ውበት ብቻ ሳይሆን፣ ለነዋሪዎቿም ንጹሕ አየር እና ለኑሮም ሆነ ለንግድ እቅስቃሴ ምቹ የሆነች እና የአእምሮ ዕረፍት የሚያደርጉባት ዘመናዊ ከተማን ፈጥሯል።
የመጋቢት ወር የከተማዋን ታሪካዊ ገጽታ ከዘመናዊው የልማት ጉዞ ጋር በማስተሳሰር፣ ውበት እና ከተሜነት የሚስተዋሉባት ከተማ የመሆኗን ጅሜሬ እንድታሳይ አስችሏታል።
በፍሬሕይወት ብርሃኑ