የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት ያሰባሰቧቸውን አጀንዳዎች የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተረከበ

You are currently viewing የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት ያሰባሰቧቸውን አጀንዳዎች የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተረከበ

AMN- መጋቢት 25/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት ያሰባሰቧቸውን አጀንዳዎች ተረከበ። ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የምክክር ሂደት ተጠናቋል።

መጋቢት 23/2018 ዓ.ም የተጀመረው የትግራይ ክልል የባለድርሻ አካላት የመጀመሪያ ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ መድረክ በሦስት ቡድኖች ተከፋፍሎ ሲከናወን ቆይቷል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ማኅበራትና ተቋማት እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች በንዑሳን ቡድኖች ተከፋፍለው አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ውይይት አጠናቅረዋል።

በውይይት የተለዩ አጀንዳዎችንም የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተረከበ ሲሆን በምክክር ጉባኤ የሚሳተፍ ተወካዮችም ተመርጠዋል።

የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱም አሳታፊና ግልጽ እንደነበር የምክክሩ ተሳታፊዎች ያነሱ ሲሆን የትግራይ ክልል በምክክር ጉባኤ እንዲቀርቡለት የሚፈለጉ አጀንዳዎች መለየታቸውንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በበኩላቸው የምክክር ሂደቱ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ያሳተፉ አጀንዳዎች የተለዩበት ነው ብለዋል።

ምንም እንኳን በክልሉ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥረው ምክክሩን በትግራይ ክልል ማካሄድ ባይችልም በዚኸኛው ዙር የአጀንዳ ማሰባሰብ የትግራይ ጉዳይ ያገባኛል በሚሉ ተሳታፊዎች በርካታ አጀንዳዎች ተለይተዋል ብለዋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review