የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኢራን የድሮን ጥቃት እንደተሰነዘረባት አስታወቀች

You are currently viewing የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከኢራን የድሮን ጥቃት እንደተሰነዘረባት አስታወቀች

AMN- ሚያዝያ 26/2018 ዓ.ም

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የአየር መከላከያ ኃይሏ ከኢራን የሚሰነዘሩ የሚሳኤል እና የድሮን ጥቃቶችን እየመከተ መሆኑን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው ፣ በመላ ሀገሪቱ የሚተኮሱ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን፣ ክሩዝ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን እያከሸፈ ይገኛል።

ከኢራን በተሰነዘረ የድሮን ጥቃት በኤምሬቶች ዋነኛ የነዳጅ ወደብ በሆነችው ፉጃይራ ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ መነሳቱን የአካባቢው ባለስልጣናትን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል።

ፉጃይራ የሀገሪቱ ትልቁ የወደብ እና የነዳጅ ማከማቻ ተቋም እንደሆነ ዘገባዎች ያመላክታሉ።

የእሳት አደጋ ሰራተኞች ቃጠሎውን ለመቆጣጠር እየተረባረቡ መሆኑን የፉጃይራ መንግስት ሚዲያ ጽ/ቤት መግለጹ ተነግሯል።

እስከ አሁን ድረስ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ሪፖርት አለመደረጉን አልጃዚራ ባወጣው ዘገባ ጠቅሷል።

ኢራን በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠችው አስተያየት የለም።

በታደሠ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review