ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአቶ ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸዉን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአቶ ዘገየ አስፋው ህልፈት የተሰማቸዉን ጥልቅ ኀዘን ገለጹ

AMN ግንቦት 4/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት አቶ ዘገየ አስፋው በማረፋቸው ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡

አቶ ዘገየ አስፋው የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በግፍ የተነጠቁት መሬት እንዲመለስለላቸውና የመሬት ሥሪት እንዲቀየር ግንባር ቀደም ሚና የተጫወቱ ናቸው።

በተለያየ ጊዜያት በሚኒስትርነት ሀገራቸውን አገልግለዋል። ከዚህም በተጨማሪ በመጨረሻው የእድሜ ዘመናቸው የሀገራችንን ነባር ችግሮች በምክክር ለመፍታት በተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት እያገለገሉ የነበሩና እጅ አጠሮችን በመደገፍ እድሜያቸውን ሙሉ ሀገራቸውን ያገለገሉ ብርቱ አባት ነበሩ።

የሰላም ዕረፍት እንዲሆንላቸው እመኛለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሃዘናቸዉን ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review