AMN ግንቦት 4/2018
ጸጥታ እና ደህንነት ለኢትዮጵያም ሆነ ለቀጠናው ሁለንተናዊ ብልጽግና ወሳኝ መሠረቶች መሆናቸዉ ተገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በሃድሰን ኢንስቲትዩት ለተመራማሪዎች ገለጻ አድርገዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ዛሬ በሃድሰን ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ታዋቂ የቲንክ ታንክ ተቋማት ከተውጣጡ ተመራማሪዎች እና የዘርፉ ኤክስፐርቶች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት እና የብልጽግና ሞዴል እንዲሁም የሀገሪቱን የፖለቲካ እይታ አቅርበዋል።

በተጨማሪም ለተሳታፊዎቹ በአፍሪካ ቀንድ ያለው የቀጠናው አሁናዊ ሁኔታ እና ጂኦፖለቲካዊ መልክ በተመለከተ ገለጻ አድርገውላቸዋል።
በውይይቱ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሲሰጡም ሚኒስትር ጌዲዮን ሰላም፣ ጸጥታ እና ደህንነት የኢትዮጵያ ራዕይ አምዶች መሆናቸውን ገልጸው ለኢትዮጵያም ሆነ ለቀጠናው ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማምጣት ወሳኝ መሠረቶች መሆናቸውን መግለጻቸዉን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።