የአዲስ አበባን ለውጥ የሚመጥን፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፀጥታ እና የደህንነት አጠባበቅ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው – ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

You are currently viewing የአዲስ አበባን ለውጥ የሚመጥን፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፀጥታ እና የደህንነት አጠባበቅ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው – ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

AMN – ግንቦት 10/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባን ለውጥ የሚመጥን፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፀጥታ እና የደህንነት አጠባበቅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ብቁ የሰው ሐይል ለማፍራት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ፡፡

ቢሮ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ለአመራሮችና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየውን የንድፈ ሐሳብና የአካል ብቃት ስልጠና የማጠቃለያና የዕውቅና መድረክ አካሄዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚህ ወቅት የአዲስ አበባን ለውጥ የሚመጥን፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የፀጥታ እና የደህንነት አጠባበቅ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ብቁ የሰው ሐይል ለማፍራት በትኩረት እየሰራ መሆን ተናግረዋል፡፡

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተቋማችን ተልዕኮ አንፃር በቂ ዝግጅት አደርገናልም ብለዋል ኃላፊዋ፡፡

ስልጠናው አቅምን የሚገነባ ሳይንሳዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሰላም እና የፀጥታ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነም ሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review