መከላከያ ሠራዊት በዓለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያተረፈ አስተማማኝ ኃይል ነው – ጄነራል አበባው ታደሰ

You are currently viewing መከላከያ ሠራዊት በዓለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያተረፈ አስተማማኝ ኃይል ነው – ጄነራል አበባው ታደሰ

AMN – ግንቦት 17/2018

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዓለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያተረፈ አስተማማኝ ኃይል መሆኑን የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ ገለጹ።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ዛሬ የ22ኛ እና የ23ኛ ሞተራይዝድ ሻለቆች፣ እንዲሁም የሶማሊያ አውሶም የሴክተር 3 እና 4 የሰላም አስከባሪ የሠራዊት አባላትና አመራሮችን አስመርቋል።

በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል አበባው ታደሰ፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊት በዓለምና በአህጉር ደረጃ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ የገዘፈ ስምና ዝና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በሰላም ማስከበር ተልዕኮ እየተመዘገበ የሚገኘውን አኩሪ ታሪክና ገድል የአሁኑም ሠራዊት በታላቅ ብቃትና ጀግንነት በማስቀጠል ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዓለም የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ታሪክ ትልቅ ስምና ዝና ያተረፈ አስተማማኝ ኃይል መሆኑን አንስተው፣ በቀጣይም ሀገርን በመወከል የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን በላቀ ብቃት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ለዚህ ታላቅ ተልዕኮ የሚሰማሩት የሠራዊቱ አባላት እና አመራሮች በወሰዱት የቅድመ ዘመቻ ሥልጠና በመመራት፣ ያላቸውን ልምድና ጀግንነት በመጠቀም፣ እንዲሁም ሕዝባዊና ወታደራዊ ዲሲፕሊንን በማክበር የተሰጣቸውን አደራ በላቀ ብቃት እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄነራል አዳምነህ መንግሥቴ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ታሪክ የራሷን የማይረሳ አሻራ ማሳረፏን አንስተው፣ አሁንም ይህንን አጠናክራ መቀጠሏን ገልጸዋል።

በእለቱ የተመረቁ የሰላም አስከባሪዎችም ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት በከፍተኛ ሥነ ምግባር፣ በሙያዊ ታማኝነት፣ በሰብአዊነትና የሀገርን ክብር በመላበስ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል አዲሱ ተርፋሳ፤ ትምህርት ቤቱ የሀገር ሉዓላዊነት እና ዳር ድንበርን በላቀ ጀግንነት እያስከበሩ የሚገኙ ጀግኖችን እያሰለጠነ ይገኛል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪም ሀገራችን በዓለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review