የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው

You are currently viewing የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው

AMN ግንቦት 18/2018

የብልፅግና ፓርቲ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍና የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር በጎንደር ከተማ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ሐሳብ የምርጫ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በተለያዩ ከተሞች እያከናወነ ይገኛል።

በጎንደር ከተማ መስቀል አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ ተንቀሳቃሽ ትዕይንተ ልማት እንዲሁም ሌሎች መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከመልዕክቶቹ መካከልም በዲጂታል ኢትዮጵያ ነገን መገንባት፣ ከዕዳ ወደ ምንዳ የተሻገረ ኢኮኖሚ፣ የኮሪደር ልማቱ የልፋታችን ውጤት የሰላማችን ዋስትና፣ ብልፅግናን መደገፍ ሀገርን መደገፍ ነው የሚሉ ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም ከትውልድ ስንፍናን እናርቃለን፣በትምህርት ኢትዮጵያን እናበለፅጋለን፣የሰላማችን መሰረት ሕብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት፣ ለሁለንተናዊ ልማትና ሰላም ምርጫችሁ ብልፅግና ይሁን! የሚሉትን ጨምሮ የተለያዩ መልዕክቶች እየተስተጋቡ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review