AMN- ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

የአርጀንቲናው የእግር ኳስ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ከአልጄሪያ ጋር ከነበረው ጨዋታ በኋላ የዓለም ዋንጫ ታሪክን በድጋሚ የፃፈ ሲሆን፣ ክብረወሰኖቹንም በመስበር የራሱ አድርጓቸዋል::
በዓለም ዋንጫ ታሪኩ የመጀመሪያውን ሀትሪክ አስመዝግቧል
በዓለም ዋንጫ መድረክ 16 ግቦችን በመረብ ላይ በማሳረፍ የጀርመኑን አጥቂ ሚሮስላቭ ክሎዘን የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ታሪካዊ ክብረወሰን በጋራ ተቆጣጥሯል።
በ 6 የተለያዩ የዓለም ዋንጫ ውድድሮች ላይ በመሰለፍ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ሆኗል።
በዓለም ዋንጫ ታሪክ ሁለት ግብ (Brace) እና ሀትሪክ የሰራ በእድሜ አንጋፋው ተጫዋች ሆኗል።
የምንጊዜም የሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫ አስገራሚ የጨዋታና የደቂቃ አኃዞች
ብዙ የዓለም ዋንጫ ውድድሮችን የተጫወተ (6)
ብዙ ጨዋታዎችን የተሰለፈ (26)
በቋሚ አሰላለፍ ብዙ ጨዋታዎችን የጀመረ (24)
በአምበልነት ቡድኑን መርቶ ብዙ ጨዋታዎችን ያደረገ (19)
በሜዳ ላይ ብዙ ደቂቃዎችን ያሳለፈ (2314+)
ብዙ ጨዋታዎችን ድል ያደረገ (17 ጨዋታዎች )
የግብና የአሲስት አኃዞች፡-
የምንጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ (16 ግቦች )
ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በብዛት ያመቻቸ / አሲስት ያደረገ (8 አሲስት – ከዲያጎ ማራዶና ጋር እኩል)
በብዙ ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያደረገ (24 ተሳትፎዎች)
በብዙ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ (12 ጨዋታዎች)
በአንድ ጨዋታ ግብ እና አሲስት በአንድ ላይ ያስመዘገበባቸው ጨዋታዎች (4 ጨዋታዎች)
የመክፈቻ ግቦችን በብዛት ያስቆጠረ (![]()
ቡድኑን መሪ የሚያደርጉ ግቦችን በብዛት ያስቆጠረ (10)
ከሳጥን ውጭ ብዙ ግቦችን ያስቆጠረ (ሁለተኛ ደረጃ – 4)
የጨዋታ ብቃትና ክህሎት አኃዞች፦
የጨዋታው ኮከብ (Man of the Match) ሽልማትን በብዛት የወሰደ (11 ጊዜ)
ብዙ ድሪብሎችን የሞከረ (188+) እና የተሳኩ ድሪብሎችን ያደረገ (112+)
ወደ ግብ ብዙ ሙከራዎችን (108+) ያደረገ ሲሆን ኢላማቸውን የጠበቁት (49+) ናቸው
ብዙ የጎል እድሎችን የፈጠረ (75+) እና ትልቅ የጎል አጋጣሚዎችን የፈጠረ (16+)
ብዙ ቁልፍ ኳሶችን ያቀበለ (75+)
በተጋጣሚ የሜዳ ክፍል ውስጥ ብዙ ትክክለኛ ኳሶችን ያቀበለ (824+)
በጨዋታ ላይ ብዙ የኳስ ንክኪዎች ያደረገ (ሁለተኛ ደረጃ – 1931+)
ሌሎች ልዩ ታሪካዊ ስኬቶች
በ5 የዓለም ዋንጫዎች ላይ አሲስት ማድረግ የቻለ እና በ4 ጨዋታዎች ላይ ግብና አሲስት በአንድ ላይ ያስመዘገበ ብቸኛው እግርኳሰኛ።
የዓለም ዋንጫ ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን ሁለት ጊዜ ያሸነፈ የመጀመሪያው እና አንጋፋው ተጫዋች (2014 እና 2022)።
በአንድ የዓለም ዋንጫ ውድድር በሁሉም 5 ዙሮች (ደረጃዎች) ላይ እንዲሁም በ5 እና 6 የተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው አርጀንቲናዊ።
በአንድ የዓለም ዋንጫ ውድድር በ3 እና 4 የተለያዩ ጨዋታዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው አርጀንቲናዊ።
በአንድ የዓለም ዋንጫ ጨዋታ ላይ ግብ እና አሲስት በአንድ ላይ ያስመዘገበ ትንሹም ታላቁም ተጫዋች።
ለአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ላይ የተጫወተ፣ ግብ ያስቆጠረ እና በአምበልነት የመራ ትንሹ ተጫዋች።
በመጀመሪያው እና በቅርብ ባስቆጠረው የዓለም ዋንጫ ግብ መካከል ትልቁ የዓመት ልዩነት ያለው ተጫዋች (20 ዓመታት)።
በብንያም ከድር