AMN- ሰኔ 11/2018 ዓ.ም

የኬፕ ቨርዴው ግብ ጠባቂ ቮዚኛ ከስፔን ጋር በተደረገው ጨዋታ አስደናቂ አቋም ማሳየቱን ተከትሎ እናቱ ጨዋታውን ተከታትላ ቢሆን ደስታው እንደነበር በእንባ ታጅቦ በመግለጹ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል፡፡

“በቪዛ ምክንያት እናቴ እዚህ ልትገኝ አልቻለችም ። መክፈል ያለብን የገንዘብ መጠን በሰዓቱ ማስተካከል አልቻልንም ነበር፣ እዚህ እንድትሆን እፈልግ ነበር” ሲል ነው ከጨዋታው በኋላ በእምባ ታጀቦ የተናገረው።
ኬፕ ቨርዴ የትራምፕ አስተዳደር ባወጣው መመሪያ መሠረት ቪዛ ለማግኘት ዜጎቻቸው እስከ 15ሺህ ዶላር የሚደርስ ዋስትና እንዲከፍሉ ከሚጠየቁ 50 አገራት መካከል አንዷ ነች።
ይህ የቮዚኛ ታሪክ የብዙዎችን ልብ ነክቶ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትም ጣልቃ በመግባት የዓለም ዋንጫ ተጫዋቾች ዘመዶች በሙሉ ከቪዛ ዋስትና ክፍያ ነፃ የመሆን መብት እንዳላቸው አረጋግጧል።
አሁን ላይ የቮዚኛ እናት አና ካንዲዳ ኤቮራ ቪዛ ማግኘታቸው የተዘገበ ሲሆን ፣ የ40 ዓመት ግብ ጠባቂ ልጃቸው ከኡራጓይ ጋር በሚያደርገው ቀጣይ ጨዋታ ላይ በስፍራው ተገኝተው ይከታተላሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ጎል ስፖርት ዘግቧል።
በታደሠ ሽፈራው