AMN ሰኔ 13/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የመሶብ ዲጂታል ማዕከል በተጀመረ በአንድ አመት ጊዜ ወስጥ ቁጥሩን 70 ማድረስ ችለናል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ ‘‘ዲጂታል ለልህቀት’’ በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት የሞባይል መተግበሪያን በይፋ መርቀው ስራ አስጀምረዋል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የመሶብ ዲጂታል ማዕከል በተጀመረ በአንድ አመት ጊዜ ወስጥ ቁጥሩን 70 ማድረስ ችለናል። በተጨማሪ የተቀሳቃሽ አገልግሎቶችም ተጀምረዋል።
የሀገራችን ኢትዮጵያ በሙስና የተተበተበ፣ ኋላ ቀር፤ ፍጥነት እና ጥራት የጎደለው፣ ዜጎችን ለእንግልት የዳረገ የአገልግሎት አሰጣጥ ታሪክ ከመሰረቱ እየተቀየረ ነው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ይህንን ችግር በመቅረፍ ከስር መሰረቱ የሚቀይር የኢትዮጵያ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎትን በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የማስፋፋት ስራ በተጀመረ በአንድ አመት ጊዜ ወስጥ ቁጥሩን ወደ 70 ማድረስ መቻል እጅግ የሚያስደንቅ ነው።
በቀጣይ በጀት ዓመት ውስጥ መንግስት ሁሉንም አገልግሎቶች ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመቀየር እየተጋ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡