AMN ሰኔ 14/2018

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን የሰጡት ድምፅ ከዜጎች የተሰጠ ታላቅ አደራ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይነት ማረጋገጫ የክብር ማህተም መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ገለጹ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ይፋ አድርጓል።
በዚህም ቦርዱ እንዳሳወቀው፤ ብልጽግና ፓርቲ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ ከተሰጠባቸው እና ውጤታቸው ይፋ ከሆኑ የምርጫ ክልሎች አብላጫ ድምጽ አግኝቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራር አባላት፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት፣ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የሲቪል ማህበራት ተወካዮችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከእያንዳንዱ ህዝብ ድምፅ የተሰጠ ታላቅ አደራ ብቻ ሳይሆን የህዝብ አገልጋይነት ማረጋገጫ የክብር ማህተም ነው ብለዋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ኢትዮጵያዊያን የሰጧቸው ድምጾችም የዕድገትና የብልፅግና ማህተም መሆናቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ በድምፁ አመኔታ የሰጣቸው የፖለቲካ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከባዱን ኃላፊነት በጸጋ በመቀበል ለህዝብ የልማት፣ የዕድገትና ብልጽግና ትሩፋት በርትተው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።