ኢትዮጵያ የተፋጠነ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እና አቅምን ያገናዘበ የአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲኖር ጠየቀች

You are currently viewing ኢትዮጵያ የተፋጠነ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እና አቅምን ያገናዘበ የአየር ንብረት ፋይናንስ እንዲኖር ጠየቀች

AMN ሰኔ 16/2018

ኢትዮጵያ የተፋጠነ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እና አቅምን ያገናዘበ የአየር ንብረት ፈንድ እንዲመቻች ጥሪ አቀረበች።

የለንደን የአየር ንብረት የድርጊት ሳምንት መካሄዱን ቀጥሏል።

በዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ (IEA) እንዲሁም በቱርኪዬ እና አውስትራሊያ (የኮፕ 31 ተባባሪ ፕሬዝዳንቶች) አዘጋጅነት ከድርጊት ሳምንቱ ጎን ለጎን ያዘጋጁት ዓለም አቀፍ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ውይይት ተካሄዷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የመጪው የ32ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP 32) ፕሬዝዳንት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ ንግግር አድርገዋል።

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በንግግራቸው፤ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማስፋፋት የሚደረጉ ጥረቶች እንዲፋጠኑና የአየር ንብረት ፋይናንስ አቅርቦት አቅምን ያገናዘበ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ ንጹህ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።

አክለውም አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለኃይል ዋስትና እና ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ወሳኝ መሠረት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የሚገጥሟቸውን የፋይናንስ ማነቆዎች ለመቅረፍ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት።

ይህንን እውን ለማድረግ የአደጋ ስጋት ቅነሳ አሠራሮችን ማስፋትና አቅምን ያገናዘበ የፋይናንስ አቅርቦትን ማመቻቸት እንደሚገባ ሚኒስትሩ ማሳሰባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ከሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በለንደን እየተካሄደ የሚገኘው የለንደን የአየር ንብረት የድርጊት ሳምንት እስከ ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review