AMN – ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር በቅንጅት ባከናወነው ወንጀልን የመከላከል ሥራ ውጤት መገኘቱ ተገለጸ።
የአዲስአበባ ከተማ የህግ ማስከበርና የመልካም አሰተዳደር ክላስተር የ2018 የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊና የክላስተሩ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በክላስተሩ በ2018 በጀት ዓመት በቅንጅት በተሰራው ወንጀልን የመከላከል ስራ ስኬታማ መሆኑን ተናግረዋል።

ክላስተሩ ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማ እንዲፈጠር ሀይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ ኩነቶች ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆኑ በመስራት የሕብረ ብሔራዊ አንድነት መገለጫ በሆነችው ከተማ የጸጥታ መዋቅሩ ከላይ እስከ ታች ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የአዲስ አበባ ሁለንተናዊ ደህንነት ላይ በስፋት ስለመሰራቱ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናግረዋል።
የክላስተሩ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በ2019 የህዝቡን ሁለንተናዊ ጥያቄ ሊመልሱ የሚችሉ በቅንጅት የተሠጡ ተልእኮዎችን ተቋማት እንደየስራ ሀላፊነታቸው ላቅ ባለና ተጨባጭ ውጤት ሊያመጣ በሚችል መልኩ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በክላስተሩ በ2018 በጀት አመት የእቅድ አፈጻም ተቋማቱ ለነበራቸው የላቀ ተሳትፎ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ጨምሮ ሌሎችም ተቋማት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል ።
በመሀመድኑር ዓሊ