ኢትዮጵያ ከማሌዥያ ጋር ያላትን ዘርፈ ብዙ ትብብር ለማጠናከር ጽኑ ፍላጎት አላት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN ሰኔ 17/2018

ኢትዮጵያ ከማሌዥያ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብር ይበልጥ ለማሳደግ እንደምትሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለማሌዥያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ባስተላለፉት መልዕክት፣ ማሌዥያ የደቡብ ንፍቀ ክበብ አጋርነትን (Global South solidarity) እና የጋራ መከባበር ራዕይን የምትጋራ ዋንኛ አጋር መሆኗን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ መሪዎች መካከል የተደረጉትን የጋራ ይፋዊ የጉብኝት ልውውጦች ያስታወሱ ሲሆን፣ በጉብኝቶቹ ወቅትም በመካከላቸው ጥልቅ መግባባት መገንባት መቻሉን ተናግረዋል።

አክለውም፣ሁለቱ ሀገራት በጋራ የጀመሯቸውን ዘርፈ ብዙ ትብብሮች ይበልጥ ወደፊት ለማስቀጠልና ለማሳደግ ኢትዮጵያ እንደምትሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review