ስዊድን እና ጃፓን ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

You are currently viewing ስዊድን እና ጃፓን ወደ ቀጣዩ ዙር አለፉ

AMN – ሰኔ 19/2018 ዓ.ም

በምድብ ስድሰት የሚገኙት ስዊድን እና ጃፓን 1ለ1 በመለያየት ተያይዘው ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።

ዴይዘን ሜኤዳ ለጃፓን አንቶኒ ኢላንጋ ደግሞ ለስዊድን ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ጃፓን አምስት ፣ ስዊድን ደግሞ አራት ነጥብ በመያዝ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ይዘው ጥሎ ማለፉን ተቀላቅለዋል።

ምድቡን በበላይነት ያጠናቀቀችው ኔዘርላንድስ ቱኒዚያን 3ለ1 አሸንፋለች።

ብሪያን ብሮቢ ፣ ፖል ቫን ሄከ እና ኤልያስ ሽሂሪ በራሱ ላይ ያስቆጠሯቸው ግቦች ኔዘርላንድስን አሸናፊ አድርገዋል።

የሮናልድ ኩመን ቡድን ሰባት ነጥብ በመያዝ ምድቡን በበላይነት ስታጠናቅቅ ፣ ቱኒዚያ ሦስቱንም ጨዋታዎች ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review