AMN – ሐምሌ 5/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የሕዝብ ትራንስፖርት ችግርን ለማቃለልና አገልግሎቱን ለማሻሻል 500 አውቶቡሶች ግዥ በሒደት ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ከንቲባዋ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡበት ወቅት ፣ ባለፉት 5 ዓመታት የከተማዋን የትራንስፖርት አቅርቦት ለማሳደግ 467 አውቶቡሶች ተገዝተው ወደ ሥራ መግባታቸውን አብራርተዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አገልግሎት የሚሰጡ የመንግሥት አውቶቡሶችን ቁጥር ከ879 ወደ 1ሺ 628 ማደጉን ጠቁመዋል።
በ2013 ዓ.ም 2ነጥብ 9 ሚሊዮን የነበረው የቀን ተጓጓዦች ቁጥር ወደ 4ነጥብ 19 ሚሊዮን ከፍ ማለቱንና የብዙሃን ትራንስፖርት የማጓጓዝ ድርሻም ከ9 በመቶ ወደ 41 በመቶ ማደጉን አብራርተዋል።

በከተማዋ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት ፍለጎት ምላሽ ለመስጠትና አገልግሎቱን ለማሻሻል የተጨማሪ 500 አውቶቡሶች ግዢ በሂደት ላይ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በወርቅነህ አቢዮ