
ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ ማስቀረቱን ሊያቆም ይገባል፤
ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን አፈናና ጭቆና ያቁም፤
ለትግራይ ሕዝብ የሚበጀው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መከበር ነው፤

ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን ወጣቶችን ያለፈቃዳቸው እያፈሰ ወደ ጦር ካምፕ በማስገባት ለዳግም እልቂት እያዘጋጀ ነው፤ ይህን ድርጊቱን የሚቃወሙ እናቶችን እያሰረ ነው፤
የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ይሁንልን፤

ሕገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ክልል እያካሄደ ያለው አፈና እና የጦርነት ዝግጅት በአስቸኳይ እንዲቆም እንፈልጋለን፤
የጦርነቱ አስከፊ ጉዳት በፕሪቶሪያ ስምምነት ቢቋጭም ቡድኑ ተግባራዊ እንዳይሆን እያሰናከለው ነው፤
ሕገ-ወጡ ቡድን ወጣቶችን ወደ ሱዳን የመሸጥ እና የግዳጅ አፈሳ ድርጊቱን በአስቸኳይ ማቆም አለበት፤

ቡድኑ በትግራይ ክልል ወጣቶች ላይ የሚፈፅመውን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልምላ እና እያደረሰ ያለውን ሰብዓዊ ጉስቁልና እንቃወማለን የሚሉና ሌሎች ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን እያደረሰ ያለውን ግፍ የሚቃወሙ መልዕክቶች በሰልፉ ተሳታፊዎች ተስተጋብተዋል፡፡
በወርቅነህ አቢዮ