የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በስኬት እየተካሄደ ነው – ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

AMN – ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ስኬታማ በሆነ መልኩ እየተካሄደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ።

ዋና ኮሚሽነሩ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሂደትን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ስኬታማ በሆነ መንገድ እየተካሄደ ነው ብለዋል።

ተመካካሪዎቹ በቡድን ተከፋፍለው በተመደቡባቸው አጀንዳዎች ላይ ውይይት ማድረግ መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም ተመካካሪዎቹ ሀሳባቸውን በነጻነት እያንሸራሸሩ እንደሆነና ይህም ለቀጣይ ምዕራፍ ውይይቶች መደላድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ በሚተላለፉ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግና ትክክለኛውን መረጃ ከኮሚሽኑ ብቻ መከታተል እንደሚገባም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ ነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review