AMN – ሐምሌ 16/2018 ዓ.ም
የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የመገናኛ ብዙኃን የዘወትር አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ገለጸ፡፡
የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የመንግስት እና የግል መገናኛ ብዙኃን ሀላፊዎች እና ሰራተኛች የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሀይማኖት ዘለቀ የአረንጓዴ አሻራ የአመራር እና የህዝብ ቅንጅታዊ ዉጤት የሀገርን ገፅታም ለአለም ያሳየ ተግባር ነዉ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለተፈጥሮ እንክብካቤ ስራ የሰጠችውን ትኩረት ለአለም ለማሳየት እና ህዝብን በንቅናቄ ለማሳተፍ መገናኛ ብዙሀን የማይተካ ሚናን መወጣታቸውንም ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ ተግባር በወቅቶች የማይገደብ ሁሉን አሳታፊ እና የተከላ ስራው ከተከላ እስከ ፅድቀት የታጀበ ይሆን ዘንድ ዘወትር መስራት ከመገናኛ ብዙኃኑ እንደሚጠበቅም ወይዘሮ ሀይማኖት ተናግረዋል፡፡

መገናኛ ብዙኃኑ ከግንዛቤ ባሻገር በተግባር ሰርቶ ማሳየት ፣ ተግብሮም ማስተማር አለበት ያሉት ኃላፊዋ የዛሬው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላም አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
የተተከሉ ችግኞች ይፀድቁ ዘንድ የእንክብካቤ ስራ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራበት ተመላክቷል፡፡
በተመስገን ይመር