አሊ አህመድ በኢትዮጵያ ያደረገውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ኖርዊች ሲቲ መደበኛ ልምምድ ተመለሰ

You are currently viewing አሊ አህመድ በኢትዮጵያ ያደረገውን ቆይታ አጠናቆ ወደ ኖርዊች ሲቲ መደበኛ ልምምድ ተመለሰ

AMN ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም

የእንግሊዝ ቻምፒዮንሺፕ ክለብ የሆነው ኖርዊች ሲቲ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጉብኝት ሲያደርግ የነበረው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አማካይ አሊ አህመድ ወደ ክለቡ የመለማመጃ ማዕከል በመመለስ ልምምድ መጀመሩን አስታውቋል።

ክለቡ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት ፤ ለቀጣዩ ውድድር ዘመን የሚያደርገውን የቅድመ-ውድድር ዝግጅት እና ልምምድ አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

ኖርዊች ሲቲ በገጹ ባሰፈረው አጭር መልእክት ተጫዋቾቹ ወደ ልምምድ መመለሳቸውን የሚያመላክት ፣ ቀጥታ ወደ ሥራ በሚል የጽሑፍ መግለጫ የአሊ አህመድን የልምምድ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ምስል አጋርቷል።

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች አሊ አህመድ፤ በኢትዮጵያ በነበረው ቆይታ በአዲስ አበባ የተለያዩ ሥፍራዎች ጉብኝት ያደረገ ሲሆን ፣ ከተለያዩ ኃላፊዎችና የስፖርት ማሕበረሰብ ጋር ውይይት በማድረግ የኢትዮጵያን ስፖርት ለመደገፍ ያለውን ፍላጎት ገልጿል፡፡

በኪዳኔ በየነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review