የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

You are currently viewing የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ

AMN ሐምሌ 27/2018

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በይፋ ተጀምሯል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትአለም መለሰ መርሐ ግብሩን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የ2018 የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመላው ኢትዮጵያ መጀመሩን አብስረዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው መሳተፍ መጀመራቸውን ያነሱት ሚንስትሯ አዲስ አበባ ከሚገኘው ከሁኔታ መከታተያ እና የመረጃ ማደራጃ ማዕከል መረጃዎች በተከታታይ ይፋ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።

ለዘንድሮው የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 853 ሚሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል።

በካሳሁን አንዱዓለም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review